የቢሾፍቱ -ጨፌ ዶንሳ-ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ

የቢሾፍቱ -ጨፌ ዶንሳ-ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ።

ይህ መንገድ 55 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 914 ሚሊየን ብር ግንባታዉ የሚከናወን ይሆናል ።

የመንገዱን ግንባታ ራማ የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ እንደሚያከናውን ተገልጿል ።

የግንባታ ስራዉ በሶስት አመታት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በይፋዊ የመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።

ግንባታው በተያዘለት የግዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የባለስልጣኑ መ/ቤት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ የተገለፀ ሲሆን በመስመሩ ያሉ የህበረተሰብ ክፍለ እና መስተደድር አካላት ለግንባታው አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንዲሰጡ ተጠይቋል።