የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እና  የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዮሪ ሙሶቬኒ  አዲስ አበባ ገቡ

የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እና  የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዮሪ ሙሶቬኒ  አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

መሪዎቹ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቶቹ ዛሬ በሚመረቀው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ለመታደም እንደመጡም ተገልጿል፡፡