ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት በልደታ የተከሏቸውን ችግኞች ተንከባከቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት በልደታ የተከሏቸውን ችግኞች ተንከባከቡ፡፡

ኢትዮጵያውያን አገራቸውን አረንጓዴ ለማድረግ እንደ አንድ ሆነው ክረምቱን በሙሉ ችግኝ ሲተክሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

እንደ ሕዝብ አረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ፣ ለዚህም ችግኞቻቸው አድገው ዛፍ እስከሚሆኑ ለመንከባከብ እና ውሀ ለማጠጣት ቃል መግባታቸውም ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በልደታ አካባቢ የተከሏቸውን ችግኞች መንከባከብ ጀምረዋል።

ችግኞቻቸውን በመንከባከብና ውኃ በማጠጣት ዛፍ ያደርጓችው ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመላ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

(ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)