በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልምድ ውስንነት የሚታይበት መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልማድም ውስንነት የሚታይበት በመሆኑ፤ ደረጃዎችን የጠበቁ ምርቶች የማምረትና የመጠቀም ባህል ማሳደግ እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎችና የአማራች ዘርፍ ባለቤቶች ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአማርች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በርካታ ቢሆኑም የዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው ያሉት ግን ከ130 አይበልጡም ተብሏል፡፡

ባጠቃላይ አሁን ላይ በአገሪቷ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልማድ ውስንነት የሚታይበት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በተለይ ከዋጋ ጋር በማነፃፀር ዝቅተኛውን የመጠቀም ልማድ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታይ መሆኑ ተነስቷል፡፡ ይህ አስተሳስብ በትምህርና ስልጠና መዳበር እንዳለበትም ነው የዘርፉ ባለሙያዎች የገለጹት፡፡

እንደ ኮርያ፣ ጃፓን እና ሲንጋፖር ያሉ ሀገራት ለእደገታቸው ቁልፍ ተደርጎ የሚወሰደው ምርቶቻቸውን በደረጃ መጠቀማቸው መሆኑን ባለሙያዎቹ በአብነት ገልጸዋል፡፡

ዓለም ያለችበትን ነባራዊና አሁናዊ ሁኔታን በማጤን እኩል መሮጥ እንዲቻል ውስጣዊ አቅም በማጎልበት በተለይ አእምሮ ላይ አና የተቋማት መሰረተ ልማት ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የሚድሮክ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የተቋማት አማካሪ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ ላይ መሰራት ያላባቸውን ጉዳዮች ቆም ብሎ በማሰብ ማበረታት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ደራጃዎች ኤጀንሲ በበኩሉ ዘርፉን ለማጠናከር በጥናትና ምርምር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መዋቅር መዘርጋቱንና ለፖሊሲና ስትራቴጂ ጠቃሚ የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እየሰራው መሆኑን አስታውቋል፡፡