የአለም ባንክና የአለም የፋይናንስ ተቋም አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን እየተካሄደ ነው

የአለም ባንክና የአለም የፋይናንስ ተቋም አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በጉባኤው እየተሳተፈ ነው፡፡

በጉባኤው በአለም ዓቀፍ ዋና ዋና የኢኮኖሚ፣ የልማት፣ የፋይናንስ፣ የድህነት ቅነሳ፣ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችና እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል።

በጉባኤው ከአለም ባንክ አባል ሀገራት የተወከሉ ከ2 ሺህ 800 በላይ ጉባያተኞችን ጨምሮ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ፣ የፋይናንስ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ከጉባኤው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ የተናጥል ውይይቶችና ስምምነቶች እንደሚደረጉ እንደሚጠበቅ ከአለም የፋይናንስ ተቋም ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡