በዓለም ባንክ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

በዓለም ባንክ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ጠየቁ፡፡

ሚኒስትሩ በዓለም ባንክ የዋሽንግተን ቢሮ ከሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በአገራችን ውስጥ እየተካሄዱ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

መንግስት አገር በቀል የኢኮኖሚ መርህ ቀርፆ ወደ ስራ ለመግባት መዘጋጀቱን፣ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ እየተሰራ መሆኑን፣ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ግንባታው ጉልህ ሚና እንዲጫወት በመንግስት በኩል ሙሉ ቁርጠኝነት መኖሩን፣ ከጎረቤት አገራት እና አለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ያለው ትብብርም እያደገ መምጣቱን ሚንስትሩ ገልጸዋል።

በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጽያዊያን ለአገራቸው እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

ሰራተኞቹም በቻሉት ሁሉ የአገራቸውን የልማት ጉዞ ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው፤ በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዳያስፖራውን አስተባብሮ ለአገር ጠቃሚ ሚናውን እንዲወጣ ከምንጊዜውም በላቀ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። (ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር