መንግሥት መልካም አስተዳድርን ለማሻሻል ወሳኝ ሚና መጫወት ይገባዋል

ሱሉልታ ፤ ሐምሌ 19/2008(ዋኢማ)–  መንግሥት  በአገሪቱ  የመልካም አስተዳደር ሁኔታ  እንዲሻሻል  ወሳኝ  ሚና  መጫወት እንደሚገባው  የሲቪል  ሰርቪስ  ቀን  በዓልን በማስመልከት በታዘጋጀው  የፓናል  ውይይት  ተመለከተ ።

10ኛው የሲቪል ሰርቪስ ቀን “ የምንመኛትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሁሉ አቀፍ ዕድገት”  በሚል  መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በሱሉልታ ከተማ  የፓናል ውይይት በማካሄድ እየተከበረ ይገኛል ።

የሲቪል ሰርቪስ ቀን በዓል ዓላማ በአገሪቱ  የፐብሊክ  ሰርቪስና  የሲቪል  ሰርቪስ የህዝብ  አገልገሎት እምነትን በማጎልበት መልካም አስተዳደርን  ከማስፈን ባሻገር   የአገሪቱን ህዳሴ  ለማረጋጋጥ የሚደረገውን ጥረት  አጠናክሮ ለማስቀጠል  መሆኑን  በፓናል  ውይይቱ ተገልጿል ።

በመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ  ያቀረቡት የአካዳሚው የሰላምና ፀጥታ ተመራማሪ ዶክተር ሃይለየሱስ ታዬ እንደገለጹት በአገሪቱ    በሲቪል  ሰርቪሱ ውስጥ  የሚስተዋሉ የአመለካከት ፣የክህሎትና አቅም  ክፍተትን አሁንም መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል ።

ሲቪል ሰርቪሱ  ይህችን  አገር  ከድህነት  ለማውጣት  በሚደረገው ሥራ  የማነሳሳት  ሚና  በመጫወት  የሲቪል ሰርቪሱ  አንድ የሥራ  አካል አድርጎ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ዶክተር  ሃይለየሱስ አስገንዝበዋል ።

በአገሪቱ  ውጤታማ የሆነ  የሲቪል ሰርቪስ አሠራርን  ተግባራዊ  ማድረግ  ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ  ሥርዓት ስኬታማነት  እጅግ  አስፈላጊ  መሆኑን  ዶክተር  ሃይለየሱስ  አመልክተዋል ።

በፓናል ውይይቱ የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ ሠራተኞች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች ፣ የአገር  ሽማግሌዎችና የተለያዩ ማህበራት  አባላት  በፓናል ውይይቱ እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

በኢፌዴሪ  የመለስ  ዜናዊ  አመራር  አካዳሚ  አዘጋጅነት እየተካሄደ  የሚገኘው   የሲቪል ሰርቪስ  ቀን በዓል  ከሐምሌ 13 እስከ ሐምሌ 20 ድረስ  በተለያዩ  ዝግጅቶች  እየተከበረ እንደሚገኝ ዋልታ  እንፎርሜሽን  ማዕከል  ዘግቧል ። 