የአጎዋ ጉባዔ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 30/2004/ ዋኢማ/-አሜሪካ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥና ኮታ ነጻ በሆነ መልኩ እንዲያስገቡ የሰጠችው ዕድል /አጎዋ/ ጉባዔ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

ኢትዮጵያ ጉባዔውን የምታስተናግደው እኤአ በ2013 ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ጉባዔውን በማስተናገድ ከዛምቢያ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር እንደምትሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ጉባዔው ከቀረጥና ኮታ ነጻ በሆኑ መልኩ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካ እንዲልኩ ዕድል የተሰጣቸው የአፍሪካ ሀገራት የልምድ ልውውጥ እንዲያካሂዱ የሚረዳ መሆኑ ተመልክቷል።

የሀገሪቱን የንግድ ስርዓት ከዓለም አቀፉ የንግድ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰርም የራሱ ሚና እንደሚኖረው ሚኒስቴሩ መግለፁን የኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ያስረዳል።