የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምርጥ አየር መንገዶች ስብሰብ የሆነው የስታር አሊያንስ 28ተኛ አባል ሆነ

አዲስ አበባ ታህሳስ 4/2004/ዋኢማ/ – የምርጥ አየር መንገድ ስብስብ የሆነው ስታር አሊያንስ እንደ አውሮፓውያኑ በ1997 ዓ.ም በዓለማችን ቀዳሚ በሆኑ አምስት አየር መንገዶች ነው የተመሰረተው በኤር ካናዳ፣ በሉፍታንዛ፣ በስካንዲቪያን አየር መንገድ በስታር ኤርዎይስ እና በዩናይትድ ኤር ላይን አማካይነት ስታር አሊያንስ አሁን በይፋ የተቀላቀለውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨምሮ 28 አባላት አሉት፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምርጦች ጥምረትን ሲቀላቀል 3ተኛው የአፍሪካ አየር መንገድ በመሆን ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካና ግብጽ አባል ከሆኑ ውለው አድረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥምረቱ አባል መሆኑ በርካታ ጥቅሞች እንደሚያስገኝለት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናግረዋል፡፡

«ኢትዮጵያ ይህን እጅግ የሚከበር እና በአለም አቀፍ ደረጃ የረዥም ጊዜ ልምድ ያለውን ጥምረት መቀላቀሏ ሌላ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡ ይህ ቀን በድምቀት የምናከብረውና በታሪክ መጽሐፋችን የሚቀር ነው፡፡ እየሰራን ያለው ስራ በፈረንጆች 2025 ያስቀመጥነው ግብ እንደምናሳካ የሚያሳይ ነው» ማለት አቶ ተወልደ ገልፀዋል።

በምርጦቹ ጥምረት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥምረቱ መረብ በአፍሪካ ዋና የንግድና የፖለቲካ ከተሞችን ለማዳረስ ያስቻለ ሲሆን፤ በተለይም በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ አፍሪካ።

በአጠቃላይ 16 የጥምረቱ አየር መንገዶች 750 ጊዜ በቀን ወደ አፍሪካ ይበራሉ፡፡ በ48 ሃገራት ከ110 በላይ ማዳረሻዎችም ይኖራቸዋል፡፡ አዲስ አበባ ካይሮ እና ጆሃንስበርግ የአገልግሎቱ እምብርት ይሆናሉ።

የምርጦቹ ጥምረት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃን አልበርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀላቀል የጥምረቱን ደንበኞች በአፍሪካ ያሉ ገበያዎችን ለመጠቀም ያስችላል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከስታር አሊያንስ መረብ ክፍል አንዱ መሆኑ ደንበኞቻችን ከአፍሪካ ጋር ለማገናኘት ትልቅ አማራጭ ይሆናል።

ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሺባ ማይል ተጠቃሚ ለነበረ ደንበኛ አሁን በሁሉም የጥምረቱ አባላት አየር መንገድ ጥቅሞችን ማግኘት እንደሚችልም አቶ ተወልደ ማስረዳታቸውን ኢሬቴድ ዘገባ ያስረዳል።