የፈደራል አቃቤ ህግ በዘጠኝ ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ መሰረተ

አዲስ አበባ፤ ጥር 01 2004 / ዋኢማ /- የፈደራል አቃቤ ህግ በዘጠኝ ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ መሰረተ።

ግለሰቦቹ አሸባሪ ተብሎ ለተፈረጀው የኦነግ ድርጅት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ቡድኑን መርተዋል፤ የሽብር ተግባሩንም አደራጅተዋል በሚል ነው አቃቤ ህግ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተባቸው።

ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን፤ የአድማ ድርጊትን የመምራትና የማሰማራት፤ የኦነግ ቡድን አባል በመሆን፣  በሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ተግባር የመፈፀም፣ በሽብር ድርጊት የመሰማራትና ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ መያዝ የሚል ክስ እንደቀረበባቸው የክስ መዝገባቸው ያስረዳል።

የክሱ ቻርጅ የደረሳቸው ተከሳሾችም

1ኛ አቶ በቀለ ገርባ

2ኛ አቶ ኡልባና ላሊሳ

3ኛ አቶ ኡልቤካ ለሚ

4ኛ አቶ አደም

5ኛ ወይዘሪት ሃዋ ዋኮ

6ኛ አቶ መሃመድ ኑሩ

7ኛ አቶ ደረጀ ከተማ

8ኛ አቶ አዲሱ እና

9ኛ አቶ ገልገሎ ጎፋ ሲሆኑ 1ኛ እና 6ኛ ተከሳሽ ጠበቃ እንደማያስፈልጋቸውና በራሳቸው እንደሚከራከሩ ያስታወቁ ሲሆን ሌሎች ተከሳሾች በተከላካይ ጠበቆቻቸው አማካኝነት የክሱ ሂደት እንዲቀጥል ተስማምተዋል።

ከተከሳሾቹ መካከል ጥቂቶቹ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲያቸውን ሽፋን በማድረግ የኦነግን ተልዕኮ ለመፈጸም እንደተሰማሩ የክስ መዝገባቸው ያስረዳል።

ተጠርጣሪዎቹ በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል የቀረበባቸውን ክስ በማስተባበላቸው አቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቹን ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ ማስደመጡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።