አንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2004 (ዋኢማ) – አንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ባጋጠመው ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ደራሲ ስብሃት ባለፈው ረቡዕ ከሆስፒታል በመውጣት ወደ ቤቱ ቢመለስም ዛሬ ንጋት ላይ ህይወቱ አልፏል።

አንጋፋው ደራሲ ህብሃት ገብረ እግዚአብሄር ትኩሳት፣ 5-6-7፣ ሌቱም አይነጋልኝንና ሌሎችንም ታዋቂ መጽሃፍት የደረሰ ሲሆን ከ19 83 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ በኋላ በአዲስ ዘመንና በሌሎችም ጋዜጦችና መጽሄቶች ላይ እጅግ በርካታ መጣጥፎችን፣ ወጎችንና ልብ ወለዶችን ጽፏል።

የደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር የቀብር ስነ ስርአት ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰአት 4 ኪሎ በሚገኘው የቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል። (ኤፍ ቢ ሲ)