ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2004 (ዋኢማ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደስታ መግለጫ አስተላለፉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለዋልታ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በላኩት መልዕክት በፑቲን አስተዳደር ሩሲያ ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት መስፈን የተለመደ ሚናዋን ትጫወታለች ብለዋል።

እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና በኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በቀጣይም በሁለቱ አገሮች መካከል የተመሠረተው ጠንካራ የመንግስት ለመንግስትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር አመልክተዋል።