የአገሪቱ የሃይል አቅርቦ ከ50 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4/2005 (ዋኢማ) – የአገሪቱ የሃይል አቅርቦት 52 በመቶ መድረሱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስር አቶ አለማዮሁ ተገኑ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በተለይ ለዋልታ ኢንፎርማሽን ማዕከል እንዳስታወቁት በአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርማሽን እቅድ አቅርቦቱን 75 በመቶ ማድረስ እንደነበር  ጠቁመው ቀሪውን 23 በመቶ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ይፈጸማል ብለዋል።

አቶ አለማዮሁ አያይዘውም ግልገል ጊቤ ሶስት፣  የህዳሴና የገናሌ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች ሲጠናቀቁ የአገሪቱ 8 ሺህ 1 መቶ 24 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ይኖራታል ብለዋል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ 23፣ ግልገል ጊቤ ሶስት 75 እና ገናሌ 30 በመቶ ግንባታቸው መጠናቀቁንም ሚኒስትሩ አቶ አለማዮሁ ተገኑ ጠቁማል።

በአገሪቱ በርካታ የገጠርና የከተማ  ቀበሌዎች በኤሌክትሪክ መረብ መገናኘታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በአስር ሺህ የሚቆጠር የማስተላለፊያ መስመርም ዝርጋታ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

ባለፉት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ቀላል የማይባሉ ተግዳራቶች እንዳጋጠሙ አስታውሰው  ችግሮቹን ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል።