25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

መጋቢት 30/2014 (ዋልታ) በኮቪድ እና በሌሎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ለሁለት ዓመት ሳይካሄድ የቆየው 25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

159 አትሌቶች የሚሳተፉበት 25ኛው የአዲስ አበባ ማራቶን ውድድር መነሻው መስቀል አደባባይ መዳረሻውን ሰሚት አደበባይ አድርጎ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ 37 የአትሌቲክስ ክለቦች እንዲሁም የግል ተወዳዳሪዎችን እንደሚሳተፉም ተጠቁሟል።

ለአሸናፊ አትሌቶች የዋንጫ እና የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።

በሚኪያስ ምትኩ