ለ16ኛው ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ/ኤድስና አባላዘር በሽታዎች ጉባዔ ምዝገባ መራዘሙ ተገለፀ

አዲስ አበባ ጥቅምት 23/2004/ዋኢማ/ – 16ኛው ዓለም አቀፍ የኤድቪ/ኤድስና አባላዘር በሽታዎች የአፍሪካ ጉባዔ ምዝገባ መራዘሙን አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ።

አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በላከው መግለጫ፤ ምዝገባው እንዲራዘም የተደረገው በጉባዔው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በጠየቁት መሰረት እስከ ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተደርጓል።

ጉባዔው ከህዳር 24 ቀን ጀምሮ እስከ 28 ድረስ የሚካሄድ መሆኑን መግለጫው ጠቁመው፤ ቀድሞ የነበረው ምዝገባም ጥቅምት 21 ቀን ይጠናቀቅ እንደነበረ መግለጫው ገልጿል።

ጉባዔውም “ባለቤትነት ማበልፀግ ዘለቄታዊነት” ወይም “Own Scale up and Sustain) በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፤ ከ10ሺ በላይ ተሳታፊዎች በጉባዔው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ እንደሚችሉ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።
ዋኢማ