አዲስ አበባ ህዳር 8/2004/ዋኢማ/ – ጠቅላይ ሚኒሰትር መለስ ዜናዊ በቻይና የንግድ ምክትል ሚኒስትር ጂያንግ ያኦፒንግ የተመራ የልዑካን ቡድንን አነጋገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እና ሚስተር ጂያንግ ያኦፒንግ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ፣ የቢዚነስ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የንግድ ምክትል ሚኒስትሩ ጂያንግ ያኦፒንግ የአሁኑ የስራ ጉብኝት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ባለፈው ነሐሴ በቻይና በመገኘት ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ያደረጉዋቸውን ዘርፈ ብዙ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመለወጥ ያለመ ነው፡፡
የልዑካን ቡድኑ የባንክ፣ የመድህን፣ የቴሌኮሙኒኬሽን የትራንስፖርትና የኃይል ማመንጫ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡
በውይይቱም የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ኢሬቴድ ገልጿል።