አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2004/ዋኢማ/ – የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዥን ፒንግ በሊቢያ አዲስ ለተመሰረተው መንግስት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ከትላንት በስቲያ በሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደል ራሂም ይፋ የተደረገውን አዲስ የመንግስት መስረታ ተከትለው የደስታ መግለጫቸውን ለሊቢያ ህዝብና ለሽግግር መንግስቱ አስተላልፈዋል፡፡
ሊቀመንበሩ እንዳሉት በሊቢያ ዲሞክራሲና ሰላም እንዲሰፍን አዲሱ መንግስት ጠንክሮ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
በተለይም በሀገሪቱ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ ህዝቡን ያሳተፈና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከናውን አንድ ደረጃ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ህብረቱም ከህዝቡና ከአዲሱ የሽግግር መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውጤታማ እንዲሆን በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ አቋም እንዳለውም ዥን ፒንግ መግለጻቸውን ህብረቱ የላከውን መግለጫ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡