787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 2/2004 (ዋልታ) – ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን የሙከራ በረራ እያደረገ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ገባ።

አውሮፕኑ የሙከራ በረራ በአፍሪካ ሲያካሂድ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜው ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች እንዲሰሩለት በማዘዝ ከአፍሪካ ቀዳሚው ሆኗል።

በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት አጋማሽም የመጀመሪያውን አውሮፕላን ይረከባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮወጋየሁ ተረፈ ለኤፍ ቢ ሲ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለእያንዳንዱ አውሮፕላን157 ሚሊየን ዶላር የመደበ ሲሆን
10ሩንም አውሮፕላኖች በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚረከብ ይጠበቃል ሲል ፋና ዘግቧል።