ኢንስቲትዩቱ በምርት ጥራት ፍተሻ ዘዴዎች ዙሪያ ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በትብብር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2004/ዋኢማ/– የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በምርት ጥራት ፍተሻ ዘዴዎች ዙሪያ ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ /IAEA/ጋር በትብብር እየሰራ ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር በአፍራሽ ባልሆኑ የጥራት ፍተሻ ዘዴዎች ዙሪያ ከዩኒቨርስቲ፣ ከፋብሪካዎች፣ ከደረጃዎች መዳቢ ኤጀንሲና ከተለያዩ ኢንስቲትዩቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎቸ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ደሳለኝ እንደገለፁት፤ ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ የምርት ጥራት ፍተሻ አይነቶች አለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት እየሰራ መሆኑን ኢሬቴድ ዘገባ ያስረዳል።

ከIAEA ጋር በትብብር መስራቱም የኢንስቲትዩቱን ሁለንተናዊ አቅም እያሳደገ መሆኑን ተገልጿል።