ቤተክርስቲያኗ ለህዳሴው ግድብ የግማሽ ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ ፈጸመች

ሀዋሳ፤ ታህሳስ 21 2004 /ዋኢማ/– የደቡብ ክልል የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የግማሽ ሚሊዮን ብር ቦንድ መግዛቷን አስታወቀች ፡፡

የሕብረቱ ሃላፊ ዶክተር ኤሊያስ ዴሌቦ እንዳስታወቁት ቤተክርስቲያኗ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የህዳሴውን ግድብ ለመደገፍ ባደረገችው ጥረት ሰሞኑን የ 573 ሺህ 367 ብር የቦንድ ግዢ ፈጽማለች፡፡

ቤተክርስቲያኗ የቦንድ ገዢውን ያካሄደችው ቀደም ሲል ለህዳሴው ግድብ ተግባራዊነት የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ በገባችው ቃል መሠረት ነዉ።በቀጣይም የህዳሴዉ ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ቤተክርስቲያኗ የጀመረችውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የቦንድ ገዢውን ያከናወነችው በሥሯ የሚገኙ 25 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን በማስተባበር ነዉ፡፡