የህዳሴን ግድብ የሚገመግመው የቴክኒክ ኮሚቴ ሱዳን ካርቱም ላይ ሊሰበሰብ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 07 2004 /ዋኢማ/ – የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተፅዕኖ የሚገመግመው የቴክኒክ ኮሚቴ ሱዳን ካርቱም ውስጥ ሊሰበሰብ ነው።

የግብፁ አል-ማስሪ አል ዮም በድረ ገፁ እንዳሰፈረው ከግብፅ፣ሱዳን እና ኢትዮጵያ የተውጣጡት የቴክኒክ ኮሚቴዎች ካርቱም ላይ የሚሰበሰቡት በመጪው እሁድ ነው።

ከሦስቱ አገራት በተጨማሪ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ አራት ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችም  ካሚቴውን ይቀላቀላሉ።

በሚቀጥለው ወር ደግሞ ኮሚቴው ግብፅ ካይሮ ላይ እንደሚገናኝ አል-ማስሪ አል ዮም በድረ ገፁ አስነብቧል።

የሦስትዮሽ ኮሚቴው ከስድስት እና ዘጠኝ ወራት በኋላ የግምገማውን ውጤት ሪፖርት ለ ሦስቱ አገሮች እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ሪፖርቱም የግድቡን ጥቅምና ጉዳት የሚያካትት ሲሆን  ሪፖርቱን ካዩ በኋላ አገራቱ በግድቡ ላይ ያላቸውን አቋም ይፋ እንደሚያደርጉ አል-ማስሪ አል ዮም ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው የተፋሰስ አገሮች ላይ ምንም ዓይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሌለው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።