የማዕከሉ ሰራተኞች የህወሓት 37ኛ ዓመት የምስረታ በአልን አከበሩ

አዲስ አበባ የካቲት 18/2004/ዋኢማ/ – የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሰራተኞች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ህወሓት/ 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በደመቀ ሁኔታ አከበሩ።

የማዕከሉ ሰራተኞች በዓሉን ባከበሩበት ወቅት የህወሓት 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ጽህፈት ቤቱ ያወጣውን መግለጫ የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና የሜጋ ማከፋፈያ የህወሓት መሰረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ ወይዘሮ አልማዝ በየነ በንባብ አቅርበዋል።

የምስረታ በዓሉ ሲከበር የጠራ ልማታዊ አስተሳብና ዴሞክራሲያዊ መስመርን በሚሊየኖች ወደሚቆጠሩ ዜጎች በማስተላለፍ መሆኑን ያብራራው መግለጫው፤ በሁሉም ዘርፍ የልማት፣ የዴሞክራሲና የሰላም እንቅስቃሴዎች ድል ሊመዘገብ የቻለው መላው ህዝብና አባላቶች የህወሓትን ጠንካራ አካሄድ መተግበር በመቻላቸው ነው።

ህወሓት /ኢህአዴግ/ ድህነትን ለማጥፋት የጀመራቸው ጥረቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስኬድ ከመላው ህዝቡና አባላቱ ጋር በመሆን የሚያደርጋቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች በተጠናከረ ሁኔታ ማስቀጠል እንደሚፈልግም መግለጫው ጠቁሟል።

ሀገሪቱ ከድህነትና ኋላ ቀርነት ተላቃ የለማችና የተከበረች እንድትሆን እየተካሄደ ያለው የልማት፣ የዴሞክራሲና የሰላም እንቅስቃሴ በጋራ ትግል ተጠናክሮ ሲሄድ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ህወሓት ልማታዊ ሰራዊት በማነፅ ልማታዊ ጉዞውን በማፋጠን ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይም የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በዓሉ ለትግሉ ውድ ህይወታቸውን ለሰጡ ታጋዮች የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፤ የሻማ ማብራትና በሌሎች ዝግጅቶች ቀርበዋል።

ለበዓሉ ድምቀትም የዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ስፖንሰር ማድረጉን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።