282 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

282 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው በትላንትናው እለት ተመልሰዋል።

የተመለሱት ሁሉም ወንወዶች ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት አስታውቋል።