የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በባህር ዳር ስብሰባውን እያካሄደ ነው

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ በባህር ዳር ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ትናንት ቀትር ላይ የጀመረው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፥ በተለይም ባለፉት 15 አመታት የተሰሩ ስራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ውይይት እያደረገ ነው።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን እንደገለፁት፥ በስብሰባው ነባር እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊው የውይይት ጊዜ የሚሠጣቸው ሲሆን፥ የ2008 እቅድ አፈፃፀምና የ2009 እቅድም የሚገመገም ይሆናል።

ኃላፊው አክለውም ኮሚቴው በሁሉም አጀንዳዎች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተለያዩ ውሳኔዎችንም ያሳልፋል ብለዋል።

እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆየው ስብሰባው ብአዴን ጥልቅ የተሓድሶ ንቅናቄውን የሚጀምርበት እንደሆነም ነው አቶ አለምነው የተናገሩት።( ኤፍቢሲ)