የኢሬቻ በዓል መስተጓጎሉንና  የሰው ህይወት መጥፋቱን  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ

የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያደረጉት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ምክንያት መስተጓጎሉን ጽ/ቤቱ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

 

በበዓሉ አከባበር ላይ አባገዳዎች በዓሉን በሰላም እየመሩ እያለ ለሁከት አስቀድመው የተዘጋጁ ኃይሎች ሁከትና ግርግር በማስነሳታቸው በዓሉ እንደተፈለገው ሳይጠናቀቅ ቀርቷል፡፡

 

ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡
 

የኢፌዴሪ መንግስት የገዳ ስርዓትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብና የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እያለ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በዚህ መልክ በመስተጓጎሉና የሰው ህይወት በመጥፋቱ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል፡፡

 

ሁከቱ በፈጠረው ግርግርና መረጋገጥ ህይወት መጥፋቱ የታወቀ ሲሆን በርካታ ተጎጂዎች ወደህክምና ቦታ ተወስደዋል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ የሚያሳውቅ ሆኖ ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ አካላትንም ለህግ እንደሚያቀርብ ቃል ይገባል፡፡