በኦሮሚያ ክልል በጥቂት ወረዳዎች ተከስቶ የነበረው ሁከት መረጋጋቱ ተገለጸ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ሠጠው መግለጫ  ከመስከረም 22 እስከ 27 2008 ዓም በክልሉ በጥቂት ወረዳዎች  ተፈጥሮ  የነበረው ሁከት መረጋጋቱን  አስታውቋል ።

ባለፈው  ሳምንት በክልሉ  የምስራቅ ሸዋ ዞን  ሰባት ወረዳዎች ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን  አምስት ወረዳዎች ፣  በምስራቅ አርሲ ዞን አራት ወረዳዎች ፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን  ሦስት  ወረዳዎችና የሰበታ ከተማ  ሁከት የተፈጠረባቸው   የክልሉ  አካባቢዎች መሆናቸው ተመልክቷል ።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን  ጉዳዮች  ጽህፈት ቤት ኃላፊ  አቶ ፈቃዱ  ተሰማ  ለጋጤጠኞች እንዳብራሩት  ባለፈው ሳምንት  የፀረ ሰላም ኃይሎች  በተለያዩ  የክልሉ አካባቢዎች በፈጠሩት  ሁከቶች  በሰው ህይወትና  በንብረት ላይ  ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል ።

የፀረ-ሰላም ኃይሎቹ  በተለይም  በኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ  ትኩረት  በማድረግ   68  የሚደርሱ  የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ  ጥቃት  ፈጽመዋል ።  በአጠቃላይ 12  የውጭና 56  የአገር  ውስጥ   የኢንቨስትመንት  ኩባንያዎች  ላይ   ጥቃቱ  ደርሷል  ።

ጥቃት  ከደረሰባቸው ኩባንያዎች መካከል  ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ውድመት የደረሰባቸው ሲሆን አራቱ  ለዝርፊያና   የተቀሩት  62  የሚሆኑት ደግሞ  በከፊል የመሰባበርና  የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሰለባ ሆነዋል ።  

የአበባ እርሻዎች  ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ድርጅቶች፣ የጨርቃ ጨርቅ ፣ ፕላስቲክና የሲሚንቶ ፋብሪካዎች  የጥቃቱ  ኢላማ  መሆናቸውን  አቶ ፈቀዱ አመልክተዋል ።

ከፋብሪካዎቹ ውጭም  የተለያዩ  መንግሥታዊና የግል ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን  አቶ  ፍቃዱ አያይዘው ገልጸዋል ።

መንግሥት   ከህብረተሰቡ   ጋር   ያደረገው  ውይይት   በክልሉ የፀረሰላም ኃይሎችን  በቁጥጥር  ሥር ለማዋልና  መረጋጋትን ለመፍጠር  እየተደረገ ላለው እንቅስቃሴ  እገዛ ማድረጉ ተጠቁሟል ።