ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ የካቢኔያቸው አባላት ለምክር ቤቱ በማቅረብ አጸደቁ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 3ኛ መደበኛው ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የቀረበሉትን የአዲስ የካቢኔ ሚንስትሮች ሹመት ምክር ቤቱ  በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምክር ቤቱ እንደገለጹት ፤ በአዲስነት ለሹመት የቀረቡት የካቢኔ አባላት፤ የትምህርት  ደረጃቸውን ፣ የአፈጻጸም ብቃታቸውንና የህዝብ ወገንተኝነታቸውን መሠረት በማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ቀደም ሲል የነበረው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ በክላስተር የማስፈጸም  እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚሉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ መቅረታቸውን  ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።

ኢህአዴግና አባል ድርጅቶቹ  መንግስት በጥልቀት የመታደስ እንስቀሴያቸው መጀመራቸውን አብስረው የመንግስት ስልጣንን ለግል ኑሮ ማመቻቻ ሳይሆን ለህብረተሰባዊ ለውጥ መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም አደረጃጀቱንና የአመራር ጥራት በየጊዜው እየፈተሹና አስፈላጊውን ማስተካከያ እያደረጉ መሄድ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡

ዲሞክራሲን የማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው የማድረግ አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ራሱን ችሎ የሚከታተል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከልና አስፈላጊ  አመራር እንዲመደብበት መደረጉን አስረድተዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው  ዘጠኝ የካቢኔ አባላትም  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት  አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አብዱል ፈታህ አብዱላሂ፣  የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬና የህዝብ  ተወካዮች  ምክር ቤት  የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አስመላሽ  ወልደስላሴ  መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

አዲስ የቀረቡት እጩ የካቢኔ አባላት የሚከተሉት መሆናቸውን በዝርዝር አመልክተዋል፡፡

1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

2. አቶ ታደሰ ጫፎ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር 

3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር 

4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ የንግድ ሚኒስትር 

5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር 

6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር 

7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 

8. አቶ አህመድ ሺዴ የትራንስፖርት ሚኒስትር 

9. ዶክተር አምባቸው መኮንን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር 

10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር 

11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር

12. አቶ ሞቱማ መቃሳ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር 

13. ዶክተር ገመዶ ዳሊ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር

14. ዶክተራው ሽፈራው ተክለማርያም የትምህርት ሚኒስትር

15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር  

16. ዶክተር ግርማ አመንቴ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር 

17. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

18. ዶክተር ደሚቱ ሃምቢሳ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር

19. አቶ ርስቱ ይርዳው የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር 

20. አቶ ከበደ ጫኔ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትር

21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ  የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር 

እነዚህም  ሹመትታቸው   የፀደቀው   የካቢኒ አባላት   በምክ ር ቤቱ    ተገኝተው  ቃለ መሃላ  ፈጽመዋል  ።   

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተጨማሪም ለተለያዩ ኃላፊዎች በሚኒስትር ደረጃ ሹመት ሰጥተዋል

1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ በየዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ፖርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች አስተባባሪ

3. አቶ ተፈራ ደርበው በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ
4. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ በማድረግ የሚኒስትር ማዕረግ ሹመት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተጨማሪም ለተለያዩ ኃላፊዎች በሚኒስትር ደረጃ ሹመት ሰጥተዋል።

1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ፡- በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ ፡- በየዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ፖርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች አስተባባሪ

3. አቶ ተፈራ ደርበው ፡- በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ
4. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር፡- በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ በማድረግ የሚኒስትር ማዕረግ ሹመት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።