መንግሥት በጥልቀት የመታደስ ተግባሩን እየፈፀመ ነው – ጽህፈት ቤቱ

የኢፌዴሪ መንግሥት እራሱን  በጥልቀት  ለማደስ  የገባው ቃል  ከፍ ባለደረጃ  እየፈጸመ መሆኑን  የመንግሥት ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው  የኢፌዴሪ  መንግሥት  ባለፉት ጥቂት ወራት  እራሱን በጥልቀት  ለማደስ  የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያካሄድ መቆየቱን አውስቷል ።

በተለይም መንግሥት  የመልካም አስተዳደር ችግር  በወጣቱ ላይ  የፈጠረውን ቅሬታ ስር ነቀል  በሆነ መልኩ  ለመፍታት  በቅልቀት  መታደስ  አስፈላጊ በመሆኑ  የመታደስ ተግባሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መግለጫ ጠቁሟል ።

መንግሥት  ባለፉት ዓመታት  የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታት ቃል ቢገባም ያገኘው ውጤት በቂ እንዳልነበረ ያተተው መግለጫው ይህም  በመንግሥት መዋቅር ውስጥ  ሥልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል ዝንባሌ በማደጉ እንደሆነ በግምገማ መረጋገጡን ተመልክቷል ።

አቅምን መሠረት ያላደረጉ ምደባዎች  በችግሮች አፈታትና በህዝብ እርካታ ማረጋገጥ ላይ እንቅፋት  መፍጠራቸውንም መንግሥት ማየት መቻሉን  ተገልጿል ።

በመሆኑም  ገዢው ፓርቲና መንግሥት በህዳሴው ጉዞው ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ለማረምም አስቀድመው  ራሳቸውን በጥልቀት  በመፈተሽ ለማጽዳት  መወሰናቸውን  መግለጫው አትቷል ።

የመንግሥት መዋቅር የህዝብ አገልጋይ እንዲሆን ለማድረግና የህዝብ እርካታን በማረጋገጥ ህዳሴውን ለማሳካት እንዲቻል በየደረጃው የሚካሄዱ ምደባዎችን በብቃትና በውጤታማነት ተመሥርቶ እንዲካሄድ በማድረግ ከጥገኝነት የፀዳ ጠንካራ መንግሥታዊ መዋቅርን መፍጠር የወቅቱ ተሃድሶው ቀዳሚ ግብ መሆኑ መግለጫው ጠቁሟል ።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ያዋቀሩት አዲሱ ካቢኔ የጥልቅ ታሃድሶው ስኬት አንዱ ማሳያ መሆኑንና  መንግሥት  ግቡን ለማሳካት  ደረጃ በደረጃ የሚያከናውናቸው ተግባራትን እያሳደገ  መምጣቱን  መግለጫው ጠቀሷል ።  

አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ ምሁራን በብቃታቸው ብቻ አገሪቱን የሚያገለግሉበት እድል ማግኘታቸውን  የገለጸው  መግለጫው ቀደም ሲል በሚኒስትርነት ደረጃ ያሉ አመራሮች

ከላይኛው መዋቅር  የተጀመረው የለውጥ ጉዞ በጥልቀት  በህዝብ ተሳትፎ እየታገዘ ወደታችኛው  መንግሥታዊ  መዋቅሮችም እንዲወርድ ይደረጋል ብሏል የጽህፈት ቤቱ መግለጫው ።

የመንግሥት ሥልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል ዝንባሌን በመድፈቅ የህዝብ አገልጋይ መዋቅርን በህዝብ የባለቤትነት መንፈስ  የተሟላ እንዲሆን በየደረጃው የሚካሄደው  ትግልም ይቀጥላል ጥገኛውንም  በማክሰም በሂደቱ  ለህዝብና አገር የሚጠቅመውን ልማታዊ ባላሃብት ተገቢውን ቦታ እንዲይዝ እገዛ እንደሚያደርግ መግለጫው አስረድቷል ።

በመጨረሻም  የጽህፈት ቤቱ  መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝቦች እንደተለመደው ከመንግስት ጎን ሆነው በንቃት በመሳተፍ በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴውን የመቋጫ ግብ እንዲያሳኩ የኢፌዴሪ መንግስት ጥሪውን አስተላልፏል ፡፡