ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ለዶናልድ ትራምፕ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዶናልድ ትራምፕ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የአሜሪካና የኢትዮጵያ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንደሚል እምነታቸውን ገልጸዋል።

ለዘመናት ለዘለቀው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

ለተመራጩ ፕሬዚዳንት መልካምና ውጤታማ የስራ ዘመን መመኘታቸውን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል-(ኤፍ.ቢ.ሲ)።