ተቀዋሚ ፓርቲዎች ለሀገራቸው ጥቅም ቅድሚያ መሰጠት አንዳለባቸው ግንባሩ አስገነዘበ

የኢትዮጵያ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ለሀገራቸው ህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መሰጠት አንዳለባቸው  የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር  አስገነዘበ ፡፡

የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ቱዋት ፓል ቻይ  እንዳስገነዘቡት ፤በኢትዮጵያ መኖር ያለባቸው ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ነው ማስቀደም የሚገባቸው  ፡፡

ተቀዋሚ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎቱ  አውቀው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል  ያሉት ሊቀመንበሩ  ፤ከሁሉም በላይ መቅደም ያለበት የኢትዮጵያ ህልውና  መሆኑን አስረድተዋል  ፡፡

ልቅና ልጓም የሌለው ዲሞክራሲ ስርዓት አልበኝነት ነው ያለት አቶ ቱዋት፤ይህ ደግሞ ስርዓትን የሚጥስ ህገ ወጥነትን የሚያስፋፋ መሆኑን  ነው ያስገነዘቡት  ፡፡

የሰለጠነ ፖለቲካዊ አቋምና አመለካከት ፣ዲስፒሊን ያለው ህብረተሰብ የመፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ፡፡

እንደዚሁም  በዲሲፒሊን የጠነከረ ሰራተኛ በኢኮኖሚ ዕድገት የሚያምን ህብረተሰብ መፍጠርም  ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

ግንባሩ ከገዢው ፓርቲ ያሉት ልዩነቶች መሰረታዊ አይይደለም ያሉት ሊቀመንበሩ ፤ያሉዋቸው ልዩነቶቹ ቢሆኑ በሂደት እየተፈቱ የሚሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል  ፡፡

ዓላማቸው የኢትጵያ ህዝብ አየተዋወቀቸው ሲሄድ  ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነታቸው በህዝብ ዘንድ ብያኔ እያገኙ መሄድ ያለባቸው በሰላማዊ ሁኔታ ነው ብሎ ድርጅታቸው እንደሚያምንም አብራርተዋል ፡፡

ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነበረች ፤በአንድ ወቅት ሁለቱም መንግስታት ወዳጆች እንደነበሩ ሁሉ አሁን ደግሞ ጠላት መሆናቸውን አንስተዋል ፡፡

ይሁንና “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” የሚል የአንዳንድ አካላት አስተሳሰብ ህዝብ እንደሚጎዳ በማወቅ ማረም አለባቸው  ነው ያሉት ፡፡

በሩብ ምዕተ ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች  መምጣታቸው ጠቅሰው፤ በዚሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የልማቱ ተጠቃሚ መሆኑን ነው ያስረዱት ፡፡

አርበኞች ግንባር በቅርቡ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋ የስምምነት ውል መፈራረሙ የሚታወቅ መሆኑን የዋልታ ዘግባ ያመለክታል ፡፡