የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላ በመላ ሀገሪቱ በሰላም መከበሩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።
የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰ የከተራ እና ጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ ያለምንም ችግር በሰላማዊ መንገድ በድምቀት ተከብረዋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረሰተቡ በተለይም ወጣቱ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች፣ ምእመናን እና የጸጥታ ሃይሎችም በዓሉ በሰላም እንዲከበር ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ህብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል(ኤፈ ቢ ሲ )።