ኮማንድ ፖስቱ ከ11 ሺህ በላይ ተሃድሶ የወሰዱ ተጠርጣሪዎች እንደሚለቀቁ አስታወቀ

በሀገሪቷ በተከሰተው ሁከት እና ግርግር ተጠርጥረው ተሃድሶ ሥልጠና የገቡ 11 ሺህ 352 ተጠርጣሪዎች በነገው ዕለት እንደሚለቀቁ የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬቴሪያት አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ገለጹ።

ሠልጣኞቹ በማዕከሉ ቆይታቸው "የተፈጠረው አመፅ አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ የኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ እንዲሁም የወጣቶች ሚና" በሚሉ ርዕሶች ላይ የተዘጋጀውን ስልጠና ወስደዋል።

 ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ስልጠና የተከታተሉ 10 ሺህ የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ተለቀው ከህብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸው ይታወሳል።

የሀገሪቷን ህልውና ለማስጠበቅ እና የሕዝብ ሠላም፣ ፀጥታ እና ደህንነት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወቃል-(ኤዜአ)።