የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ኢትዮጵያ ድርቅን ለመቋቋም እያደረገቸው ያለው ጥረት ሊታገዝ እንደሚገባው ገለጸ፡፡
ኢትዮጵያ ያጋጠማት ድርቅ ከፍተኛነቱ የምስራቅ አፍሪካ አገራት እንኳን በጋራ ሊቋቋሙት የሚያዳግታቸው በመሆኑ ሀገሪቷ ድጋፍ ሊደረግላት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልጸዋል፡፡
በአየር መዛባት ምክንያት እየተከሰተ ያለው ድረቅ ተደጋጋሚነቱና አስከፊነቱ ቀላል እንደማይባል ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡
ሰላምና መረጋጋትን ለማስከበር በየአገራቱ የሚደረገው ጥረት ድርቅን ለመቋቋም በሚደረገው ጥረት ላይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ሰናይ ተግባር ነው ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
ድርቅ የግጭትና ስደት መስፋፋት ምክንያት ሊሆን እንደሚችልና ኢትዮጵያ ከዚህ አንጻር ያረጋገጠችውን ሰላምና መረጋጋት አስጠብቃ መቀጠል እንዳለባትም ጠቁመዋል፡፡
ጉቴሬዝ አያይዘውም አገራት ድርቅን ለመከከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ ብቻ ሳይሆን ሰላም፣ መረጋጋትና ዘላቂ ልማትን በማፋጠን ላይ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ እንዲያጠናክሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡