የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ተወካይ እና ከአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሚስ ፌደሪካ ሞገህሪኒ ጋር መከሩ።
ምክክሩ የተደረገው ከሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ ጎን ለጎን ሲሆን ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነትን ፣ ፍልሰትን እና ኢትዮጵያ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት የምታደረገውን ጥረት አስመልክቶ ውይይት ተደረጓል።
በዚህም መሰረት፣ በሶማሊያ የተደረገው ምርጫ ከአገር ግንባታ ጥረቶች ጋር ሲታይ አበረታች እንደሆነ፣ ኢትዮጵዮጵያና ኢጋድ ይህን ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በሶማሊያ ተቋማዊ ግንባታን ለመደገፍ እና ሰላማና መረጋጋትን ለማምጣት ከሶማሊያ መንግስት ጋር እንደሚሰሩ አስታውቀው፤ የአውሮፓ ህብረትም ይህንኑ ጥረት እንደሚደግፍ እምነታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሚስ ፌደሪካ ሞገህሪኒ በበኩላቸው ቀጠናዊ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የፍልሰት ጉዳዮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ትብብር የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል። መንግስት የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት ሚስ ፌደሪካ ሞገህሪኒ አድንቀዋል። (ው/ጉ/ሚ)