አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኤል ሲሲ አቀረቡ ።
በካይሮ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለግብፅ ዓረብ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ አቅርበዋል።
የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ ፕሬዝዳንት ኤል ሲሲ የሹመት ደብዳቤውን በተቀበሉበት ስነ-ስርዓት ላይ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ እንደምትሻ ገልጿል ነው ያለው ።
የአምባሳደር ታዬ መሾም በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ግንኙነት መዳበር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው ያመለከቱት ።
አምባሳደር ታዬ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት እንዳለ አንስተው በስራ ቆይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማዳበር የግብፅ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ድጋፍ እንደማይለያቸው ተስፋቸውን ገልጸዋል ።