29 አባዎራዎችን የሚያስጠቅም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመረቀ

ሐምሌ 9/2014 (ዋልታ) በኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የተገነባ ባለ አምስት ወለል የጋራ መኖሪያ ቤት ተመረቀ።
የጋራ መኖሪያ ቤቱ 29 አባዎራችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
የጋራ መኖሪያ ቤቱን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቦታው ለተነሱ 19 አባዎራዎች በእጣ አከፋፍለዋል።
እጣ ለወጣላቸው 19 አባዎራዎች የመኖሪያ ቤት ቁልፍ አስረክበዋል።
ከንቲባ አዳነች ምንጊዜም ሕዝባችን ለሰጠን አደራ 24 ሰዓት እንሰራለን ብለዋል።
በትእግስት ዘላለም