ኦማር ሃሰን አልበሽር የሶስት ቀናት የኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት ያደረጉትን የሥራ ጉብኝት  አጠናቀው ወደ አገራቸው  ተመለሱ።

ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ይበልጥ ተባብራ ለመስራት ያላትን ፅኑ ፍላጎት የገለፁ ሲሆን ይህ ትብብር ከሁለቱ ሃገራት ባለፈ ለቀጠናው መረጋጋት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡

ፕሬዚደንት አልበሽር  በጉብኝታቸው  ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ይበልጥ  ተባብራ ለመሥራት ጽኑ እምነትና ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል ።

የሱዳንና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ከሁለቱ አገራት ባለፈ ለቀጠናው  መረጋጋት  ቁልፍ  ሚና  እየተጫወተ እንደሚገኝ  ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ  መለስ አለም  የአልበሽርን ጉብኝት አስመልክተው ለዋሚኮ በሠጡት አስተያያት እንደገለጹት ፕሬዚደንት አልበሽር በጉብኝታቸው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም  ጋር ተወያይተዋል።

እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ሱዳንና ኢትዮጵያ ዘመናት ያስቆጠረ ወዳጅነትን የመሠረቱ አገራት መሆናቸውንና የአገራቱን ግንኙነት  ወደ መደበኛ ትብብር ለመቀየር  ውይይት አድርገዋል ።

የሱዳን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሠማራት በቁጥር በሦስተኛ  ደረጃ ላይ እንደሚገኙ  ቃልአቀባዩ ጠቁመዋል ።

የሁለቱ አገራት የኢኮኖሚ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ  በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ  መቃረቧን፣  የአዲስ አበባ -ካርቱም የአውቶቢስ ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩንና የመሠረት ልማት ትስስሩ መጠናከሩን ቃልአቀባዩ በአብነት ጠቅሰዋል ።