ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት አመለካከትና ተግባራት ቀጣይ ትግል ሊደረግባቸው እንደሚገባም አፅንኦት መስጠቱን ኢህአዴግ አስገነዘበ ፡፡
የኢህአዴግ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ስብሰባ ማጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ እንዳለው በውይይቱ በጥልቀት የመታደስ የንቅናቄ መድረኮች በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት መፈፀማቸውን ገምግሟል፡፡
የኪራይ ሰብሳቢነት ወኪል ሆኑት የትምክህትና ጠባብነት አመለካከትና ተግባራት ሀገራችን በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንድትቆም አስገድደዋት እንደነበር ገምግሟል ፡፡
ምክር ቤቱ በተቀጣጣለው የተሃድሶ ንቅናቄ አስከፊውን ሁኔታ በመቀልበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን በመጥቀስ፡፡
ከዚህም በላይ በአመራርና በአባላት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት፤ በሲቪል ሰርቫንቱና በህዝቡ ዘንድም የተነሱ ችግሮች ይፈታሉ የሚል ተስፋ አሳድሯል ብሏል፡፡
በአጠቃላይ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው ባለፉት 15 የተሃድሶ ዓመታት በልማት፣ በሰላም እና በዴሞክራሲ መስኮች የተመዘገቡ አንጸባራቂ ድሎች ላይ ህዝቡ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረውም የጋራ መግባባት ተፈጥሮበታል ነው ያለው ፡፡
በሌላ በኩል የኪራይ ሰብሳቢነት ወኪል የሆኑት የትምክህትና ጠባብነት አመለካከቶችና ተግባራት የፌዴራላዊ ዴምክራሲያዊ ስርዓታችን ዋነኛ አደጋ መሆናቸውን የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው መሆኑን አመልክቷል ፡፡
በቀጣይ ትግል የህዳሴ ጉዞውን ማደናቀፍ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ በማድረስ ሀገራዊ ህዳሴውን እውን ለማድረግ ድርጅት፣ ሲቪል ሰርቫንቱ እና ህዝቡ ለለውጥ መነሳሳታቸውን ምክር ቤቱ መገምገሙንም መገለጫው አመልክቷል፡፡
ኢህአዴግ በጥልቅ ተሃድሶው ከተቀመጡት አቅጣጫዎች አንዱ ድርጅትና መንግስትን መልሶ ማደራጀት ነበር ብሏል ፡፡
ከዚህ አኳያም መልሶ የማደራጀቱ ተግባር ከላይ እስከ ታች ባሉ የድርጅትና የመንግስት መዋቅሮችን ቁርጠኝነቱና ተነሳሽነቱ ባላቸው አመራሮች መልሶ የማደራጀት ስራው መከናወኑን ገምግሟል፡፡
ምክር ቤቱ በአመራር ስምሪቱ ላይ ህዝቡ ቀጥተኛና ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎውን ባረጋገጠ አኳሃን አመራሮችን እየተቸ ያገለግሉኛል የሚላቸውን ይሁንታ እየሰጠ አያገለግሉኝም የሚላቸው ደግሞ በአመራርነት እንዳይቀጥሉ ያደረገበት እንደነበር ጠቅሷል ፡፡
ይህ ሁኔታም ህዝቡ የስልጣን ባለቤትነቱን ያረጋገጠበት ከመሆኑም በላይ ለቀጣይም ይኸው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክር ቤቱ አስምሮበታል ብሏል ፡፡