ኢዴፓን ጨምሮ ያለ ሶስተኛ ወገን አንደራደርም ሲሉ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን ቀይረው ያለአደራዳሪ ለመከራከር ተስማሙ ፡፡
ኢዴፓ እና መኢአድን ጨምሮ የስድስቱ ፓርቲዎች በዛሬው እለት በሶስተኛ ወገን በአደራዳሪነት ያስፈልጋል የሚለውን ሃሳባቸውን ማንሳታቸውን አስታውቀዋል ፡፡
እነዚህ ለበርካታ ዙሮች ሲያቅማሙ የነበሩ አዴፓ፣ መኢአድ ፣ሰማያዊ ፓርቲ ፣ኢብኢን፣መኢዴፓ እና ኢራፓ ያለአደራዳሪ አጀንዳዎቻቸው ላይ ለመወያየት አንፈልግም ሲሉ መቆየታቸው ይታወቃል ፡፡
እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድሩ በዙር ይካሄድ የሚለውን አቋማቸውንም ማንሳታቸውንም ገልጸዋል ።
ባለፈው ሳምንት አዴፓና መኢአድ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ ዕድል እንዲሰጣቸው በመጠየቅ “እዚህ ያለነው ሰዎች ጨርሰን መወሰን አንችልም ፤ስለሆነም በቀጣይ ሳምንት የፓርቲዎቻችንን ስራ አስፈጻሚ አካላትና መላ አባላቶቻችን ጋር መክረንና ተወያይተን ያለአደራዳሪ እንቀጥላለን ወይስ አንቀጥልም የሚለውን መጥተን እንሳውቃለን” ማለታቸው አይዘነጋም ፡፡
በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ “በዓለም ላይ ያለአደራዳሪ የሚካሄድ ድርድር ስለሌለ መደራደር አንፈልግም!” ሲሉ ማስታወቃቸውንም እንዲሁ ፡፡
እንዲያውም ሊቀመንበሩ “ያለአደራዳሪ የሚደረገውን ውይይት የገፋው ራሱ ኢህአዴግ ስለሆነ አንቀበለውም፤ ያለአደራዳሪ የሚቀጥል ከሆነ ግን ተመልሰን ልንወያይ እንችላለን” የሚል አቋማቸውን መግለጻቸውን ይታወሳል ፡፡
ኢህአዴግ ያለአደራዳሪ ለመወያየትና ለመከራከር የወሰኑትን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አብሮ ለመቀጠል ያረጋገጠ ሲሆን ምናልባት ያለ ሶስተኛ ወገን እንደራደርም ያሉ ፓርቲዎች ዕድሉ ሊጠቀሙበት ከፈለጉ በሩ ክፍት መሆኑን አሳስቦም እንደነበርም ዋልታ በዘገባው መግሉ ይታወቃል ፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከመድረክ በስተቀር ድርድሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች በቋሚነት በሚመረጡ አደራዳሪዎች ይመራ ወይንስ በዙር የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይምሩት በሚለው ጉዳይ ላይ ፓርቲዎቹ ክርክር እያካሄዱ ናቸው ።
በዚሁ ስ8ኛ ዙር ውይይት ሀገር አቀፍ ፓርቲዎቹ በድርድር አሰራር እና አካሄድ ረቂቅ ደንብ ላይ በመወያየት ላይ ይገኛሉ ።
በሰባተኛው ዙር ኢህአዴግን ጨምሮ 13 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለአደራዳሪ የሚል አቋም ይዘው ሲደራደሩ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው ።