ምክር ቤቱ ጥልቅ ተሃድሶው በጥራት መካሄዱን አስታወቀ

በመላ አገሪቱ  በኢህአዴግ  መሪነት ለወራቶች ሲካሄድ የቆየው  ጥልቅ ተሃድሶው  ሂደት ጥራቱን  በጠበቀ  ሁኔታ  መከናወኑን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ ።

የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለዋሚኮ እንደገለጹት የኢህአዴግ ምክር ቤት ባለፉት 15 ዓመታት  በአገር ደረጃ  የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በጥልቅ ገምግሟል ።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም  በዘንድሮ ዓመት  በአገሪቱ በየደረጃው የተከናወነው  የመታደስ ሂደት  በጥራት  መካሄድ መቻሉን አረጋግጧል ብለዋል አቶ ሽፈራው ።

ባለፉት ወራት የተካሄደው ጥልቅ ተሃድሶው በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን ስጋት መቀልበስ ያስቻለ መሆኑን  አቶ ሽፈራው ጠቁመዋል ።

የኢህአዴግ ምክር ቤት በጥልቅ ግምገማውም ሆነ በሰሞኑ ግምገማ ባስቀመጠው አቅጣጫ የመልካም አስተዳደር፣ ያልተገባ ጥቅም ፈላጊነትና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ በቀጣይ ትኩረት  የሚሠጥባቸው ጉዳዮች መሆኑን ማስታወቁን አቶ ሽፈራው አመልክተዋል ።        

ምክር ቤቱ  የመልካም አስተዳደር ችግርን ፣ ያልተገባ ጥቅም ፈላጊነት አባዜንና  የወጣቶች የሥራ ማጣት ችግር  ለመፍታት  በፍጥነት ተጨባጭ እንቅስቃሴ ውስጥ መገባት እንደሚያስፈልግ አጽዕኖት መሥጠቱን ዋልታ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ዘግቧል ።