በአሜሪካ ህግን በመጣስ ለ12 ዓመት ያህል በሴቶች ላይ ግርዛት የፈፀሙት ዶክተር የዕድሜ ልክ ዕስራት ይጠብቃቸዋል ተባለ፡፡
ዶክተር ጁማና ናጋርዋላ የተባሉት የህክምና ባለሙያ በስድስትና በስምንት ዓመት የዕድሜ ክልል በሚገኙ ሴቶች ላይ ግርዛት ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይህ ድርጊታቸውም ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ፡፡
ዶክተሯ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በዕድሜ ልክ እስራት ህይወታቸውን በሙሉ በማረሚያ ቤት ሊያሳርፉ ይችላል ተብሏል፡፡
የሴቶች ግርዛት በአሜሪካ እአአ ከ1996 ጀምሮ በህገ ወጥነት መደንገጉን ዘገባው አመልክቶ ግለሰቧ ድርጊቱን አለመፈፀማቸውን መናገራቸውን አመልክቷል፡፡
የአሜሪካ ተጠባባቂ ዐቃቤ ህግ ዳንኤል ሌሚሽ በአሜሪካ የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶች ላይ ጥቃትን እንደመፈፀም እንደሚቆጠር ጠቁመው በወንጀልም እንደሚስጠይቅ ነው ያስረዱት፡፡
በፈረንጆቹ 2012 በአሜሪካ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሴቶች ለግርዛትና ለተያያዥ ጥቃት እንደሚጋለጡ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡