ምክርቤቱ ከተለያዩ አገራት በጋራ ትብብሮች የተስማማባቸውን ለቋሚ ኮሚቴዎች መራ

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ከተለያዩ አገራት በልማት፣በህልና በግብርና ትብብሮች የተስማማባቸውን ረቂቅ አዋጆች ለቋሚ ኮሚቴዎች መምራቱን አስታወቀ ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሰት ከሱዳን መንግሰት ጋር በመንገድ፣ በአየር ትራንሰፖርት፣ በደን ልማት ጥበቃ እና ቁጥጥር ዙሪያ ያደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል ፡፡

እንዲሁም መንግስት ከጋቦን፣ ከጋናና ከኮሞሮስ ጋር የጠቅላላ ትብብር ለማድረግ የተስማማባቸው ረቂቅ አዋጆችም እንዲሁ ፡፡

በቱሪዝም ዘርፍ ከአልጄሪያ ጋር፣ በባህል ዘርፍ ከኬንያ ጋር በግብርና ዘርፍ ደግሞ ከኩዌት ጋር የተደረጉ ስምምነቶችም በዝርዝር እንዲታዩ ነው የወሰነው ፡፡

ከጁቢቲና ኬንያ ጋር ደግሞ የባቡር ሃዲድ መስመር ዝርጋታን አስመልክቶ መንግስት ከሃገሪቱ ጋር በረቂቅ አዋጅ የተስማማው ለቋሚ ኮሚቴዎች ለዝርዝር እይታ ነው የላከው ፡፡

ከኮሪያና ከአየርላንድ ጋር የአየር ትራንስፖርት ስምምነትም በተመሳሳይ ቋሚ ኮሚቴዎች ይመልከቱት ብሏል ምክርቤቱ ፡፡