ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የፍትህ ጉዳይ ላይ ተሳትፎ እንዲያርግና ለፍትህ ስርዓቱ መጎልበት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ተባለ፡፡
ሰባተኛው ሀገር አቀፍ የፍትህ ሳምንት “የህግ የበላይነት ለዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አንድነት” በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 30 ጀምሮ ይከበራል፡፡
የዘንድሮው መሪ ቃል የተመረጠው የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ቀዳሚ ጉዳይ የህግ የበላይነትን ማስከበር በመሆኑ ነው ብለዋል የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ፡፡
የበዓሉ መከበር የፍትህ አካላት ከተደራሽነት፣ ከቀልጣፋነትና ውጤታማነት አንፃር እየሰሩ ያለው ስራ ይበልጥ አመርቂ እንዲሆን መደላድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡
የፍትህ ሳምንት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ይከበራል፡፡ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረኮች ፣ አውደ ርዕዮች፣ በእግር ጎዞ በዓሉ ይከበራል፡፡
ከሚያዚያ አስራ አራት ጀምሮ በሚካሄደው የፍትህ ሳምንት አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ከሰማኒያ ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የሚያሳትፍ የፍትህ ሳምንት ንቅናቄ እንደሚካሄድ ተገልጿል ፡፡