ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው የገቡ 15 ሽብርተኞች  ተያዙ

ከኤርትራ ሰርገው የገቡ 15 የግንቦት ሰባትና የኦነግ ሽብር ቡድን አባላት የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ጸጥትና አስተዳደር አስታወቀ ፡፡

በኤርትራ በኩል የሽብር ተልዕኮ ይዘው ወደ ማኸል ሃገር ለመግባት የሞከሩ 15 የጸረ ሰላም ሃይሎች ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በያዝነው ሳምንት ብቻ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ጸጥታና አስተዳደር ኃላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ ገልጸዋል ፡፡

የጸረ ሰላም ኃይሎቹ በኤርትራ ከሚኖረው የግንቦት ሰባትና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር  (ኦነግ) የሽብር ቡድን ተግባር ተልዕኮ ይዘው የገቡ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

የሽብር ቡድን አባላቱ የተያዙት በአከባቢው በንቃት በሚጠብቁት በመከላከያ ሰራዊትና በዞኑ ነዋሪዎች በተደረገ ጠንካራ የክትትል ስራ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የሽብር ቡድን አባላቱ ወደ መሃል ሃገር በመግባት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት ላይ አደጋ ለማድረስ ከሽብር ቡድኑ ተልዕኮ የተቀበሉ እንደነበሩም ነው የገለጹት፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በአጠቃላይ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሸልኮው ወደ መኻል አገር ሊገቡ የነበሩ 98 ጸረ ሰላም ሃይሎች በቁጥጥር ስር በመዋላቸው ያሰቡት እኩይ የጥፋት ዓላማቸው መክሸፉን ኃላፊው አስታውቀዋል-(ኤፍ ቢ ሲ) ።