ኢትዮጵያ 120 እስረኞችን ለመልቀቅ መስማማቷን ሱማሊያ አስታወቀች  

ኢትዮጵያ ከ120 በላይ ሱማሊያውያን አስረኞችን ለመልቀቅ መስማማቷን የሱማሊያ ጠቅላይ መኒስተር ሓሰን ዓሊ ካይረ አስታውቀዋል ፡፡

የሱማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በቲውተር ገጻቸው በለቀቁት መረጃ እንዳገለጹት፤ በ29ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ለመገኘት አዲስ አበባ በቆዩባቸው ቀናት ከኢትዮጵያ መንግስት ባደረጉት ውይይት እስረኞችን ለማስለቀቅ የተሳካ ስራ ማከናወናቸውን ነው  ፡፡

ከእስር ከሚለቀቁት ውስጥም በሽበርተኝነት ዘገባ ላይ ተሰማርቶ በመገኘቱ ለበርካታ ዓመታት ተፈርዶበት የነበረው የሱማሊያ ጋዜጠኛ በቆራቃ በርታማሃ አንድሚገኝበት ጠቁመዋል ፡፡

ከእስር የሚፈቱ እስረኞችም ምናልባት ወደ ሱማሊያ ሞቃዲሾ እንደሚሄዱ ነው የተመለከተው ፡፡

ምናልባትም አንዳንዳንዶቹም የእስር ጊዜያቸው በሀገራቸው በሱማሊያ ላይ እንደሚጨርሱም ይገመታል ፡፡

 ምንጭ -The East Affrica