2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ዛሬ ይጀመራል

2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) ዛሬ 2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት የጋራ ኃላፊነት! እንወቅ! እንጠንቀቅ!” በሚል መሪ ቃል መከበር እንደሚጀምር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስም በተለያዩ ስነ-ሥርዓቶች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

በዓሉን በዋናነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በማዘጋጀትና በማስተባበር የሚመራው ሲሆን፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ይሳተፉበታል፡፡

የሳይበር ደህንነት ወር መከበር ዓለማም ”የሳይበር ማህበረሰቡን እና ተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት የሚያስችል ንቅናቄን በማካሄድና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን የማስጠበቅ ተልዕኮ ማገዝ” መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡