300 ዜጎች ከሳዑዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

የካቲት 04/2013 (ዋልታ) – ሶስት መቶ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገነኘው መረጃ አመላክቷል።