300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ተመለሱ

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – 300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ከጂዳ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።