የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዚዳንቶችን ሾሙ

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች መሾማቸው ተገለጸ ።

የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል  እንደተናገሩት ፥ ለሁለቱ ባንኮች አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች ሹመት ተሠጥቷል።

አቶ ባጫ ጊኒ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል  ።

አቶ ባጫ ቀደም ሲል የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉ ናቸው ።

እንዲሁም  አቶ ኃይለኢየሱስ በቀለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳነት ሆነው ተሾመዋል።

አቶ ሃይለኢየሱስ የባንኩ ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ጌታሁን ናናን በመተካት   ነው የልማት ባንክ ፕሬዚደንት  ሆነው  የተመደቡት ።

አቶ ኃይለየሱስ በቀለ የቀድሞው ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው።