የጨፌ ኦሮሚያ 8ኛ መደበኛ ጉባዔ ከሃምሌ 2 ጀምሮ ይካሄዳል

የጨፌ ኦሮሚያ 8ኛው መደበኛ ጉባዔ ከሐምሌ 2 እስከ ሐምሌ 4 ፤2010 በአዳማ የጨፌ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ጨፌው በሚቀርቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 1 ፤2010 በቡድን ውይይት እንደሚያደርግም ተገልጿል።    

ጨፌው በሚያካሄደው መደበኛ ጉባዔ የሥራ አስፈጻሚ አካላት 2010 አፈጻጸም ሪፖርትና 2011 እቅድ፣ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች 2010 አፈጻጸም ሪፖርትና 2011 እቅድ፣የኦሮሚያ ኦዲት መሥሪያ ቤት 2010 አፈጻጸም ሪፖርትና 2011 እቅድ እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት 2010 አፈጻጸም ሪፖርት እና 2011 እቅድ ውይይት ከሚደረጉባቸው አጀንዳዎች ይገኙባቸዋል።  

በሌላ በኩል ጨፌው 2010 በጀት ዓመት የበጀት ጭማሪ አዋጅ ፣የ2011 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጀት እና የተለያዩ ሹመቶችን ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡  (ኢዜአ)